473 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 209 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

473 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 209 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ 473 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው ሰዎች 209 ደግሞ ማገጋቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ባለፉት 24 ሰዓታት 5 ሺህ 589 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

በዚህም 473 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 105 ሺህ 352 ደርሷል።

የዛሬዎቹን 209 ሰዎች ጨምሮ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 65 ሺህ 534 ሆኗል።

ከዚህ ባለፈም የ16 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 636 ደርሷል።

በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 591ሺህ 148 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

The post 473 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 209 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply