You are currently viewing 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን ሰኞ ይካሄዳል

5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን ሰኞ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ሰኞ ያካሂዳል፡፡

ምክር ቤቱ ስብሰባውን የሚያካሂደው በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው ተብሏል፡፡

በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው፡፡

እንዲሁም የግብርና፣ አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሰኞ እንደሚካሄድም ይጠበቃል፡፡

ቋሚ ኮሚቴዎቹ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በምክር ቤቱ ጉባዔ አዳራሽ ስብሰባቸውን ያካሂዳሉ ነው የተባለው፡፡

The post 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን ሰኞ ይካሄዳል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply