575 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል

575 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 676 የላቦራቶሪ ምርመራ 575 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 91 ሺህ 693 ደርሷል።

በ24 ሰዓታቱ 754 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በዚህም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 45 ሺህ 260 ደርሷል።

እንዲሁም ከቫይረሱ ጋር ተያይዞ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉ የተገለፀ ሲሆን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እስካሁን በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 396 መድረሱ ተጠቁሟል።

306 ያህል ሰዎች ደግሞ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸውም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post 575 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply