6ኛው ‘አግሮ ፉድ ፕላስት ፕሪንት ፓክ’ ኢትዮጲያ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ተከፈተፕራና ኢቨንትስ እና የጀርመኑ ‘ፌርትሬድ’ በጋራ ያዘጋጁት ይህ መድረክ በግብርና፣ በምግብና መጠጥ ግብዓት…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/EIjOj6KLnz17jxPwr4S5H0IY4JXTPg5-fTJ8I2TWrQSgsGyVCZBdeqGvVmr_VacF6xSM0U0zZsPkpCZ8MgZe9LuBSG_0gAM5sU_hvwjcS-Cz9xRZml6R_Kurf13iLouaPTEUcKVpPotlCkOOGkKVHwrxbO-P36DN4pFUfcX2F9q75wmM1Qcro5aKuNtwtYd7cfSuDWyvPWOI2Uxvuh2Hbe3iCPOXhLlOb-655dGrOymC8pXg3q5D0vHDtCY0QbQTjH0NnoMDD-_JoOejzyxwkutAVCrlYO0nSg_pnxrbEq6nN1x_TVrzctnEpOqIpeBKIVcfe22iyiTile9bqLOMbQ.jpg

6ኛው ‘አግሮ ፉድ ፕላስት ፕሪንት ፓክ’ ኢትዮጲያ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ተከፈተ

ፕራና ኢቨንትስ እና የጀርመኑ ‘ፌርትሬድ’ በጋራ ያዘጋጁት ይህ መድረክ በግብርና፣ በምግብና መጠጥ ግብዓትና ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም በፕላስቲክ ህትመት እና የማሸጊያ ቴክኖሎጂ እና መፍትሄዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ትርኢት እንደሆነም ተገልጿል።

በመክፈቻ መድረኩ የተገኙት የኢንዱስትሪ  ሚኒስትር  አቶ ሀሰን መሀመድ እንደዚህ አይነት ትርኢቶች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውበዘርፉ የተሰማሩ ሀገር በቀል አልሚዎችን ምርታቸውን በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲያስተዋውቁ እድል የሚሰጥ እንዲሁም ከተለያዩ ቢዝነስ ሴክተሮች ጋር ልምድ የሚፈጥሩበት እንደሆነ ተናግረዋል።

በትርኢቱም የቱርክ፣ የቻይና እና የህንድ ብሄራዊ ተሳትፎን ጨምሮ ከ12 አገራት የተውጣጡ ከ120 በላይ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት እንደሆነም ተገልጿል

በዚህ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት የገበያ ትስስር ሰንሰለት፣ ዓለም አቀፍ ግብይት እና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሽግግር እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

የንግድ ትርኢቱም በሚሊኒየም አዳራሽ ለአገልግሎት ክፍት እንደሆነ ተነስቶ  ከግንቦት 8 ቀን ጀምሮ እስከ 10 ቀን 2016 ድረስ  እንደሚቆይም ተነግሯል።

ለአለም አሰፋ 
ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply