በአሁኑ ሰዓት ይህንን የቀዶ ህክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሳሪያ እንደሌለውም ሆስፒታሉ አስታውቋል፡፡
በአይደር ሆስፒታል በአሁኑ ጊዜ በከባድ ሀኔታ ውስጥ ሆነው ቀዶ ህክምና አገልግሎት ፈልገው የሚጠባበቁ ታካሚዎች ከ6ሺህ በላይ ቢሆኑም ህክምናውን ግን መስጠት አልተቻለም ሲሉ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አብርሃ ገብረመድህን ለኢቲዮ ኤፍ ኤም ገልጸዋል፡፡
ላለፉት 2 አመታት ያክል በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ሲካሄድ የቆየውን ጦርነት ተከትሎ በርካታ የጤና ተቋማት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ይህም ከሰላም ስምምነቱ በኋላ እየተሰሩ ካሉ መልሶ ግንባታዎች ውስጥ የሚጠቃለል መሆኑ ይታወቃል፡፡
በትግራይ ክልል ካሉት ሆስፒታሎች መካከል ትልቁ የሆነውና በመቀሌ ከተማ የሚገኘው የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታልም በጦርነቱ ምክንያት የደረሰበትን ጉዳት ተከትሎ መልሶ እንዲቋቋም በማድረግ ረገድ ያሉት ስራዎች እጅግ አዝጋሚ መሆናቸውንም ለጣቢያችን አንስተዋል፡፡
አሁን ላይ አንገብጋቢ የሚባል እና በቂ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ረገድ አዳጋች ሁኔታ እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በቀዶ ጥገና እና ሌሎችም ክፍሎች የሚያገለግሉ እንደ ኤም አር አይ (MRI) አገልግሎት መስተት ማቆሙን የነገሩን ሲሆን ለዚህ ደግሞ ለሚጠገኑ እና ለሚቀየሩ ክፍሎቹ 32 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ነግረውናል፡፡
በተጨማሪም በድንገተኛ ፣ በእናቶችና ህጻናት ፣ በቀዶ ጥገና እና ሌሎችም ክፍሎች የሚያገለግሉ እንደ ኤም አር አይ (MRI) ፣ አልትራሳውንድ ፣ ኦክስጅንና የመሳሰሉት መሳሪያዎች ብልሽት እንዲሁም እጥረት ማጋጠሙን የገለጹት ዶክተር አብርሃ ችግሩ እንዲፈታ ለጤና ሚኒስቴር ጥያቄ መቅረቡንም ተናግረዋል፡፡
አንዳንዶቹ መሳሪያዎች ደግሞ በጊዜ መተካት እያለባቸው ቶሎ ባለመቀየራቸው ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እስከማቆም መድረሳቸውንም አንስተዋል፡፡
በረድኤት ገበየሁ
ሐምሌ 07 ቀን 2015 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Source: Link to the Post