629 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል

629 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7 ሺህ 454 የላቦራቶሪ ምርመራ 629 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።

በዚህም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 92 ሺህ 858 ደርሷል።

በሌላ በኩል በ24 ሰዓታት 724 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በዚህም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 46 ሺህ 842 ደርሷል።

እንዲሁም ከቫይረሱ ጋር ተያይዞ የ19 ሰዎች ህይወት ማለፉ የተገለፀ ሲሆን÷ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እስካሁን በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 419 መድረሱ ተጠቁሟል።

306 ያህል ሰዎች ደግሞ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸውም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

The post 629 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply