7ኛው የኢትዮ ኸልዝ አውደርዕይ ሊካሄድ ነው::7ኛው የኢትዮ ኸልዝ ዓለም አቀፍ አውደርዕይ እና ጉባኤ ከየካቲት16 — 18/2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡በ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/QhO3NdOH0Vo6OncfH-OE48ydp2SkHRwUFIAAnuzxpWm8uhlXfCivLfGwg9UaPUvC_QiAtkHmgmJiVHXtce6KsKKokxEOXJXDlNougP3PKQOUU2LXP_g0C5hstGfgeMZS3c9qD8Ny0XPd7_aGB85NAc5x1rghteE6EeEnF-rs8Uqm7RR_oYS4ZWlmkDgj-P7g3r4DgZNEtb2twExPrMM9-5RVZu_hMrEa5IdDOTAWjR0_NYh2fjj57JjTcQbn7u7LMzUy4GQ3SK-DebuyiTbfYHOkgODnSM-IsQLrWGj-_SV1tmVbZ8qAWwABGpHXsO1mg7xPFhMMyv-_UHrmDmO80g.jpg

7ኛው የኢትዮ ኸልዝ አውደርዕይ ሊካሄድ ነው::
7ኛው የኢትዮ ኸልዝ ዓለም አቀፍ አውደርዕይ እና ጉባኤ ከየካቲት16 — 18/2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

በዚህ ዓውደ ርዕይ ከዘጠኝ አገራት የተውጣጡ ከ4 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች እና የዘርፉ የንግድ ባለድርሻ አካላት፣ከ100 በላይ ዓለም አቀፍ የዘርፉ መሪዎች እና ስመጥር የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር የንግድ ትስስር ያደርጋሉ ተብሏል።

በዚህም በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ያለውን የህክምና አገልግሎት ፍላጎት ለማሳካት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂ እና መፍትሄዎችን የሚያቀርቡ ከበ9 ሀገራት መሰረታቸውን ያደረጉ ኩባኒያዎች ከአውደርዕዩ ጎብኚዎች ጋር እንደሚወያዩም ተጠቁሟል።

በዚህ ጉባኤ 11 የሙያ ማህበራት ማለትም የኢትዮጵያ ሀኪሞች ማህበር ፣የኢትዮጵያ ልብ ሀኪሞች ማህበር፣ የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ሀኪሞች ማህበር ፤ የኢትዮጵያ ኢኒስቶሎጂስቶች ማህበር ፣ የኢትዮጵያ ቀዶ ጥገና ሀኪሞች ማህበር ፣ የኢትዮጵያ ራዲዮሎጂሶሳይቲ፣የኢትዮጵያ ፋርማሲ ባለሙያዎች ማህበር፣ የኢትዮጵያ ራዲዮ ቴክኖሎጂስቶች ማህበር ይሳተፋሉ ተብሏል።

ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርኢትና ዓውደ ርዕዮችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ፕራና ኢቨንትስ ከ11 የሙያ ማኅበራት ጋር በመተባበር በስድስት ጉባኤዎች ለዘረፉ ባለሙያዎች ተከታታይ የሙያ ማጎልበቻ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ የፕራና ኢቨንት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነብዩ ለማ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች ማህበር፣ የኢትዮጵያ ባዮ ሜዲካል ኢንጂነሮች እና ቴክኖሎጂስቶች ማህበር፣ የኢትዮጵያ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር እንዲሁም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ እና የጤና ወግ የጉባኤው አጋር መሆናቸው ተነግሯል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
የካቲት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply