70 የሚሆኑ ዓለም አቀፍ ፕሮጀክቶችና 165 የሚሆኑ የምርመራ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን የሐዋሳ ዩንቨርስቲ አስታወቀ፡፡

የ45 ዓመታት እድሜ ያለው የሐዋሳ ዩንቨርስቲ በጥናትና ምርመር መስክ በተለይም የአካባቢውን ማህበረሰብ በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ስራዎችን እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡የዩንቨርስቲው የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ታፈሰ ማቲዎስ ለአሀዱ እንደተናገሩት ተቋማቸው ሀገራዊ ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ 165 የሚሆኑ የምርምር ስራዎችን መንግስት በጀት ይዞላቸው እያከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ዩንቨርስቲው 12 የቴክኖሎጂ መንደር ተብለው የተለዩ ወረዳዎች እንዳሉት የገለፁት አቶ ታፈሰ በእነዚህ ቦታዎች ላይ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ በሰብልና በእንሰሳት እርባታ መስክ ያተኮሩ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በማቅረብ ላይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የከተመባትን የሐዋሳ ከተማና አካባቢውን በአረንጓዴ ልማት ለመሸፈን ዩንቨርሰቲው እየሰራ ነው ያሉት የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንቱ እንደ ሀገር ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የአረንጓዴ ልማት ዘመቻ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል፡፡

ቀን 12/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply