700 የሚደርሱ ተማሪዎች “በባህርዳር እንደቤቴ ” መርሃግብር የገናን በዓል አሳልፈዋል፡፡ (አሻራ ጥር 1፣ 2013 ዓ.ም) በ2010 ዓ.ም የተጀመረው የባህርዳር እንደቤቴ መርሃግብር በዘንድሮ…

700 የሚደርሱ ተማሪዎች “በባህርዳር እንደቤቴ ” መርሃግብር የገናን በዓል አሳልፈዋል፡፡ (አሻራ ጥር 1፣ 2013 ዓ.ም) በ2010 ዓ.ም የተጀመረው የባህርዳር እንደቤቴ መርሃግብር በዘንድሮው ገና 700 የባህርዳር ዮኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ገናን እንደ ቤተሰብ ማዋል ችሏል፡፡ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ባህርዳር ያለ ተማሪ የኛ ልጅ ነው፣ ከተለያዮ የሀገሪቱ ክፍል የሚመጡ ተማሪዎችም ባህርዳር ቤታቸው ነው በሚል ሀሳብ የተጀመረው ቤተሰባዊ ትስስር በዘንድሮው ገናም ደምቆ ውሏል፡፡ 400 ተማሪዎች ከባላደራ ወላጆቻቸው ቤት ገናን አክብረዋል፡፡ ባለ አደራ ወላጆች ተማሪዎችን እንደ ወላጅ በዓልን በጋራ ሰብስበው ከማክበር ባሻገር፣በከተማው ሲኖሩ ምንም ነገር እንዳይገጥማቸው ክትትል እና ድጋፍ ያደርጉላቸዋል፡፡ ተማሪዎችም እንደ ባላአደራ ወላጅ በመመልከት በዓልን በጋራ ያሳልፋሉ፡፡ ምርቃታቸውንም ከባላደራ ወላጆች ቤት ያደርጋሉ፡፡ 300 የሚደርሱ የባህርዳር ዮኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ደግሞ የባህርዳር ከተማ ወጣቶች በድብ አንበሳ የገና የምሳ ግብዣ በማድረግ ባህርዳር የእናንተ ናት፡፡ ቤተሰብ ነን ብለዋቸዋል፡፡ በአጠቃላይ 700 ያህል ተማሪዎች ባህርዳር ቤታችሁ ፣ስትኖሩ እንደ ከተማችሁ፣ ኗሪዎችም እንደ ቤተሰቦቻችሁ ቁጠሩ ተብለዋል፡፡ ከተለያዮ አካባቢ የመጡ ተማሪዎችም በባህርዳር እንደቤቴ መርሃግብር ተደስተው የአመፅ እና የአፈና ማዕከል የሆኑ ዮኒቨርሲቲዎች ከባህርዳር እንደቤቴ ልምድ ይውሰዱ ሲሉ ምክራቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ወደ ዮኒቨርሲቲ ስንመጣ ወቅቱ አመፅ የበዛበት ስለሆነ ችግር ይገጥመናል ብለን የተወሰነ ብንሰጋም በባህርዳር መኖር ግን ከእናት ጓዳ እንደመኖር ሰላም እና ምቾት አለው ብለዋል ተማሪዎች፡፡ ከተማ አስተዳድሩ በበኩሉ፣ በባህርዳር በየትኛውም ሰዓት ለሚንቀሳቀሱ ጎብኝዎችም ሆኑ ሌሎች ፣ የደንብ ማስከበር ስራዓቱ ጠንካራ እና የተናበቡ በመሆኑ ችግር አይገጥማቸውም ፡፡ ባህርዳር ከተፈጥሮአዊ ውበቷ በላይ በሰላሟ እና በእንግዳ አክባሪነቷ መለዮ እንዲኖራት ከተማ አስተዳድሩ ይሰራል ተብሏል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply