80 በመቶ ሰብሎች መሰብሰባቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊከሰት እንደሚችል መጠቆሙን ተከትሎ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ አርሶ አደሮች እንዳይዘናጉና ሰብሎችን በወቅቱ እንዲሰበሰቡ ከክልል ግብርና ቢሮዎች ጋር በጋራ የተጠናከሩ ስራዎች መስራታቸውን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡

ከክልል ቢሮዎችና ከአርሶ አደሮች ጋር በመነጋገር በተሰሩ ስራዎች ከትግራይ ክልል ውጭ በአብዛሃኛው የሀገሪቱ ክፍል ባሉ አካባቢዎች 80 በመቶ የሚሆኑ ሰብሎች መሰብሰብ መቻሉን የግብርና ሚኒስቴ የሰብል ልማት ዳሬክተር አቶ ኢያሳያስ ለማ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ በኦሮሚያ ክልል በባሌና በአርሲ ዞን በሲዳማ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች አንዳንድ ያልደረሱ ሰብሎች መኖራቸውን ተከትሎ ያልተሰበሰቡ ምርቶችን መኖራቸውን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪ በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ችግሮች ምክንያት ለአርሶ አደሮች የሰብል አሰባሰብ ላይ ተፅእኖ ያሳደረ ሲሆን አሁን ላይ ሰብሎችን የማጨድ ስራ መጀመራቸውን አቶ ኢሳያስ አንስተው በሚቀጥለው ሳምንት ያለበትን ደረጃ እንደሚያሳውቁ አስታውቀዋል፡፡

*************************************************************************************

ዘጋቢ፡አብርሃም አያሌው

ቀን 20/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply