81ኛው የአርበኞች ቀን መታሰቢያ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡እለቱን አስመልክቶም የእንኳን አደረሳችሁ፤አደረሰን መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እለቱን አስመልክተዉ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/rZ-i_wk0hgyF6jQ_0JdQ0_RmwsBG0nB__rLeRUMsAB4vyWC48HvvbYNJtdYOzTAbF6dVHy-AfvIJg7lwmsl-vFSmz5GdfGcaINDd5PfDGQCMWcNOQpamUzPL1E_rlWSwKRzB4hrUfx_jUMy6eOGGeU5KBlvkv0pkXERZ_TXGRMwGx-2JwnJc8en_p7VG-RnJw8EYVhK3bGBzD9Hh4awFZHIHN5WGQPfh6qoiewyWbH5KeLPYgogNHLhN0EaMUfyuEs2ic9cDenIlRCXEiuDm1vnR8aRr4RHDlSk8khxrJhLkVwpyRijnhsKOEM54pGb-ERY34Ii-VHLFjH1k7fjUHg.jpg

81ኛው የአርበኞች ቀን መታሰቢያ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

እለቱን አስመልክቶም የእንኳን አደረሳችሁ፤አደረሰን መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እለቱን አስመልክተዉ ባስተላለፉት መልዕክት ዐርበኝነት ማለት በሀገር ጉዳይ ላይ ለእውነትና ለእምነት የሚከፈል መሥዋዕትነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጀግኖች እናቶቻችን እና አባቶቻችን የሀገራቸውን ነጻነትና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሲሉ ምትክ የሌለውን ሕይወታቸውን መክፈላቸውን አስታውሰዋል።

ዛሬ ይሄንን የሕይወት ዋጋ የከፈሉትን ዐርበኞቻችንን በክብር እናስባቸዋለን ነው ያሉት።

እኛም ልጆቻቸው፣ ቀደምት ዐርበኞች ላከበሯት ሀገራችን ልዕልናና ብልጽግና ለማጎናጸፍ ዋጋ የምንከፍል ተተኪ ዐርበኞች መሆናችንን ልናረጋግጥ ይገባናልም ብለዋል በመልዕክታቸው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸዉ፤የአርበኞች ቀንን በልዩ ትኩረት እና ክብደት የምንዘክረው ጀግኖች አርበኞች ለሃገር አንድነት እና ሉዐላዊነት መከበር የከፈሉትን ዋጋ በትውልዱ ዘንድ ተምሳሌታዊ የድል አድራጊነት መንፈስ እንዲጋባ በማሰብ መሆኑን አንስተዋል።

በተለይ ጀግኖች አርበኞች ሀገራችንን ከወራሪ ጠላት ለመጠበቅ በዱር በገደል በመዋደቅ እና አኩሪ ገድል በመፈፀም በትውልድ ቅብብሎሽ የድል አድራጊነት ዘላቂ ፈለግ አውርሰው ማለፋቸውንም አብራርተዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply