81 + 47 በአንድ ጀንበር የተረሸኑ *************************** ተጠርጥራችኋል ተብለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ትዕዛዝ በክልሉ ልዩ ኃይል ታፍሰው በእስር ቤት እንዲቆዩ…

81 + 47 በአንድ ጀንበር የተረሸኑ *************************** ተጠርጥራችኋል ተብለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ትዕዛዝ በክልሉ ልዩ ኃይል ታፍሰው በእስር ቤት እንዲቆዩ ከተደረጉት የአማራ ተወላጆች መካከል ከስር ስማቸው የተዘረዘሩትን ሕዳር 19/2015 ለህዳር 20 ከእስር ቤት አውጥተው ረሽነዋቸዋል። 1ኛ. ኡመር አሊ… 2ኛ. ወርቂት ሙሀመድ 3ኛ. መዲና ከማል 4ኛ. አህመድ ከማል 5ኛ. ጦይብ ከማል 6ኛ. ሼህ ከማል በድሩ 7ኛ. ኢብራሂም አሊ 8ኛ. ሙሀመድ አሊ 9ኛ. ታጁ መሀመድ 10ኛ. ሙሀመድ ዳውድ 11ኛ አስናቀው እባቡ 12ኛ. ተመስገን መልክ ነው 13ኛ. ሳኒ ከማል 14ኛ. መሀመድ ከማል 15ኛ አህመድ ከማል 16ኛ. ዚነት ሰይድ 17ኛ. ሰሚራ ሰይድ 18ኛ. ሽኩር ሙሀመድ 19ኛ. ፋጢማ ጅብሪላ 20ኛ. አስናቀው ካሳው 21ኛ. ዩኑስ ሙሀመድ 22ኛ. ኡመር ሙሀመድ 23ኛ. ጥላሁን ዘነበ 24ኛ. ኢስማኤል ደሳለኝ ከዚህ በታች ያሉት ደግሞ ከነ ቤተሰቦቻቸው የተረሸኑ ሲሆኑ፦ 1ኛ. ጀማል ዳምጤ እሱን ጨምሮ 5 የቤተሰብ አባላቱ 2ኛ. አበባው መኮነን እሱን ጨምሮ 6 የቤተሰብ አባላቱ 3ኛ. ሼህ ሙሳ የሱፍ እሱን ጨምሮ 5 የቤተሰብ አባላቱ 4ኛ. ቃሲም ሲራጅ እሱን ጨምሮ 3 የቤተሰብ አባላቱ 5ኛ. ከማል ፈድሉ ከነ ባለቤቱ ቤተሰቦች ጨምሮ 21 የቤተሰብ አባላቱ 6ኛ. ሙሳ አሊ እሱን ጨምሮ 7 የቤተሰብ አባላቱ 7ኛ. አሊ ሀሰን እሱን ጨምሮ 10 የቤተሰብ አባላቱ ናቸው። እነዚህ በእስር ላይ እንዳሉ የተረሸኑት 81. ሰዎች የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ሕዳር 9 እና ህዳር 20/2015 ዓ/ም ቤት ለቤት እየዞሩ ከገደሏቸው 47 የአማራ ተወላጆች ተጨማሪ መሆናቸውን ማረጋገጫ የሰጡት ከአሰቃቂው ግድያ የተረፉ የአይን እማኝ ምስክሮች ናቸው። ******** ዛሬ ማለዳ 11:30 የጀመረው የጉትን ወረዳ … ዘግናኙ አማራን የመጨፍጨፍ የዘር ማፅዳት ወንጀል እንደቀጠለ ነው። እልቂቱን ለመሸፋፈን የእርስ በእርስ ግጭት እንዳለ ለማስመሰል እነ ጃዋር ጭምር እየጻፉ ይገኛሉ። አማራውን በሰቅጣጭ ሁኔታ ከጨፈጨፉ በኋላ መሰል ማደናገሪያ በማንሳት ለማዳፈን የመሞከር ስልት ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ እንደ ስልት የተያዘና የቀጠለ ሆኗል። ምንጭ ሀብታሙ አያሌው

Source: Link to the Post

Leave a Reply