829 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባለት ከዳርፉር ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ ነው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 27፣ 2013 ዓ.ም) በሱዳን ዳርፉር ግዛት ከ14 ዓመት በፊት በተነሳ የጎሳ ግጭት ከ30…

829 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባለት ከዳርፉር ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ ነው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 27፣ 2013 ዓ.ም) በሱዳን ዳርፉር ግዛት ከ14 ዓመት በፊት በተነሳ የጎሳ ግጭት ከ300 ሺ በላይ ሱዳናውያን ሙተዋል፡፡ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሱዳናውያን ተፈናቅለዋል፡፡ ይህም የአልበሽርን አስተዳድር በጦር ወንጀል አስከስሶት ነበር፡፡ … ከ13 ዓመት በፊት የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ ህብረት በዳርፉር ወታደር አሰማርቶ የሱዳንን የእርስ በእርስ አልቂት አስታገሰ፡፡ በዚህ ውስጥ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት ቁጥር በዳርፉር አሰማርታለች፡፡ አሁን ቀነ ገደቡ ተጠናቀቀ፡፡ ሱዳንም የራሴን ሰላም አስከብራለሁ አለች፡፡ ኢትዮጵያም 829 ወታደሮቿን ልትመልስ እንደሆነ ሪፖርተር እንግሊዘኛው እትም አስነብቧል፡፡ ኢትዮጵያ ሰሜን እና ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያን በማረጋጋት ተኪ የለሽ ሚና ተጫውታለች፡፡ ሱዳን ግን ኢትዮጵያ የውስጥ ችግር ውስጥ በወደቀችበት ሁኔታ ከኢትዮጵያ ድንበር 30 ኪሜ ገብታ ወራለች፡፡ ሁለት ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት አውድማለች፡፡ አሁንም ሱዳን ምሽግ እየቆፈረች እና የወረረችውን ለማፅናት እየሞከረች ነው፡፡ ኢትዮጵያም ዝምታዋን አብዝታለች፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply