83.3 ሚሊዮን ሰዎች በኮቪድ-19 ተጋልጠዋል 1.8 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው አጥተዋል

https://gdb.voanews.com/fd226508-fc18-4583-9d46-ce7e9515bb8c_cx0_cy6_cw0_w800_h450.jpg

አዲሱ የአውሮፓውያን 2021 በገባበት በዚህ ወቅት፣ በመላው ዓለም 83.5 ሰዎች ለኮቪድ-19 የተጋለጡ ሲሆን፣ 1.8 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ፣ በወረርሽኙ መሞታቸውን፣ የጆን ሀፕኪንስ የኮሮና ቫይረስ የምርምርና ዕለታዊ የመረጃ ማዕከል በበዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የመረጃ ማዕከሉ እንዳስታወቀው ዩናይትድ ስቴትስ በወረርሽኙ ተጠቂዎች አሁንም ከፍተኛውን ደረጃ ይዛለች። ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ አሜሪካውያን ለቫይረሱ ሲጋለጡ ከ345 ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ ህይታቸውን አጥተዋል፡፡

እንደ ጆን ሀፕኪንስ ገለጻ ህንድ ለቫይረሱ የተጋለጡ 10.2 ሚሊዮን ሰዎች አሏት። 148 ሺሕ ሰዎች በወረርሽኑ ህይወታቸውን በማጣታቸው ሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ባለፈው ሐሙስ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ የባዮቴክ ስሪት የሆነውና ፋይዘር የተሰኘውን የኮንረና ቫይረስ ክትባት፣ ለአጣዳፊ ችግሮ መጠቀም የሚቻል መሆኑን በመፍቅድ ታዳጊ አገሮች ክትባቱን በቶሎ የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸቱን አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ክትባቱን የሙቀቱ መጠን ከ70 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች በሆኑ ማቀዝቀዣ ቦታዎች ማስቀመጥን፣ በብርቱ ጥንቃቄ ማጓጓዝና ስርጭቱንም ለማቀላጠፍ ከፍተኛ አቅምን የሚጠይቅ በመሆኑ ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ተገምቷል፡፡

የቻይና ባለስልጣናት የቻይና መድሃኒት አምራቾች ላበለፀጉትና ለአገሪቱ የመጀመሪያ ለሆነው የኮቪድ ክትባት ፈቃድ ሰጠ። የመንግሥቱ ብሔራዊ የመድሃኒት ምርቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ዛሬ ሐሙስ ይፋ እንዳደረገው፤ በመንግስቱ ሲኖፋርም ለተያዘው የቤጂንግ የመድሃኒት አምራች ኢንሲቲዩት ፍቃድ የተሰጠው ክትባቱ 79.3 በመቶ ቫይረሱን የመቋቋም አቅም እንዳለው ከተረጋገጠ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የውጭ ባለሞያዎች ሲኖፋርም ላይ ጥያቄ እያስነሱ ይገኛሉ። ምክኒያቱም ክትባቱ በገለልተኛ አካል ሊረጋገጥ የሚያስችለውን አስፈላጊ መረጃዎች አላቀረበም ብለውታል።

አዲሱ ፍቃድ የተሰጠውና አምስት ኩባንያዎች ያመረቱት የቻይናው ክትባት አሁንም ለሶስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ ቢሆንም እስካህን 4.5 ሚሊዮን ሰዎች እንዲከተቡት ተደርጓል።

አስትራዚንካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በጋራ በመተባበር ያበለፀጉት የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ብሪታንያ ፈቃዷን የሰጠችው አዲሱ ክትባትም በብዛት መታዘዘ ጀመሯል።

የፋይዘር ባዮቴክ ክትባትን ጨምሮ ኮቪድ-19ኝን ለመዋጋት በመረት ላይ ያሉት ክትባቶች ኮሮናቫይረስ ወደ 1.8 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት በመላው ዓለም በቀጠፈበት በዚህ የ2020 ማጠናቀቂያ ወቅት መልካም ዜና ናቸው ተብለዋል።

በሌላ በኩል የካሊፎርኒያ የጤና ባለስልጣናት በብሪታኒያ የታየው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ በካሊፎርኒያ በአንድ ሰው ላይ መታየቱን አስታውቀዋል ምናልባትም በሌሎች ሰዎች ላይ ሳይኖር አይቀርም ሲሉ ጥርጣሬያቸውን አጋርተዋል። አዲሱ ቫይረስ በዩናይትድስቴትስ ሲታይ ባለፈው ሳምንት በኮሎራዶ ከታየው ቀጥሎ ሁለተኛው ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply