84ኛው የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ዓመታዊ በዓል በእንጅባራ ከተማ እየተከበረ ነው። በዓሉ”የሰላም አርበኝነት ለወንድማማችነት”በሚል መሪ ሀሳብ ነው በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የሚገኘው፡፡…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/YI2GNS2AIj2qjZVhpSngsC8hElXo6Ki2pAP3cIYxLTf8hyd8IG2P4A2xUFUq69MsjEaQmTb0oB1xjAXriXZIPAhi20Ji43lj2RSVfZgiQEpn2fqtl5Rb5nxdpS14gW3TKAO4Jv92de-WBDN1EKl4d6u0DBu9dOW6MLu0NvFmRKEceOlqLbGuL3R5YJEG3tQ5QYxSFc27WXpUIWXIYMykm_-wXZPZxgEeEaaYDUvCNM7qWKmtqjzVaAq4oeUuMljljqKVxwSZ8Us9qGmHvdAAWHj1AyiCzQ583LL2IyB-MJFf5SZkK_VrhSoQWQFxfc9F_m8Dxetg5dFqE4oXCG-CBw.jpg

84ኛው የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ዓመታዊ በዓል በእንጅባራ ከተማ እየተከበረ ነው።

በዓሉ”የሰላም አርበኝነት ለወንድማማችነት”በሚል መሪ ሀሳብ ነው በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በአከባበር ሥነ- ሥርዓቱ የአማራ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዱ ሁሴን፣ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ፣ ሌሎች የክልሉ የሥራ ሃላፊዎች እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

የአገው ፈረሰኞች ማኅበር የብሔረሰቡ አባቶች ከሌሎች አርበኞች ጋር በመተባበር የጣልያንን ወራሪ ጦር ዓድዋ ላይ ድል መቀዳጀታቸውን ለመዘከር በየዓመቱ ጥር 23 የሚከበር በዓል ነው፡፡

አሁን ላይም በብሔረሰብ አስተዳደሩ የሚገኙ የባህል ቡድን አባላት የተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎችን እያሳዩ መሆኑን የአዊ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply