85 ሚሊዮን ናይጄሪያውያን ሥራ ሊያጡ እንደሚችሉ ተገለፀ።

የናይጄሪያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው  እንደገለፁት 85 ሚሊዮን ናይጄሪያውያን በዲጂታል እውቀት እና ክህሎቶች እጥረት ምክንያት ስራቸውን ሊያጡ እንደሆነ ነው ፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በ2030 ሀያ ሚሊዮን  ናይጄሪያውያን ወጣቶችን  ስራ ለማስያዝ ያለውን ዕቅድ በገለፁበት መድረክ ነው ፡፡

እንደ ተቋም  በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ወጣቶችን ወደ ሥራ ለማስገባት ብድር አንደሚያመቻቹ ያስታወቁ ሲሆን

በሂደትም በክልሉ ውስጥ  ለ ዲጂታል  ትምህርት ማስተማሪያ የሚሆን ማዕከል ለመገንባት  የ‹በ7 ቢሊዮን ዶላር  በጀት መመደቡን ገልጸዋል፤ ይህም‹ ወጣቶች ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በሚያደርግ ምርምር ላይ የተመሠረተ ነው ›ሲሉ ተደምጠዋል ፡፡

ምንጭ፡- የኦል አፍሪካን ነው

ቀን 21/11/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply