9 አመታት የፈጀው የሙዚቃ አልበም ሊወጣ ነው።ማያዬ የተሰኝው የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል የመጀመሪያ አልበም የፊታችን አርብ ይለቀቃል ተብሏል።ድምፃዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል የመጀመሪያ አልበሟ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Z0oM_HPBbBGTm9jbeOa3yoG-K1LdutXl2qvYYhUQsYeQ-ZPnwLG8oBkyoFfvUmv6f4RIXwwMlaq3QRGtRmEqYh6A4-9Gng4vKFt1o5QvmY8JPSNpc-BlRkdshQIP27RWDO97Q4wT9LuMKwfCatBlfKg2AZn7Rg_Jjbtk-XXYdlyFOqHit3QCeG_mycgDie5IeZe3faV8zIH9Yhbn0uQ0MWFI6kvkXC44aiJqH45r8OTozcl7sWnIC80LqcFCYoU8CGCtloLyCpTMqBp_KPhjOClTW8SLllgp0joSFtL9MfEjlfgHoIyvt06QaIcAWKNXzgiEsQU2EJwqzbfUBIHjSg.jpg

9 አመታት የፈጀው የሙዚቃ አልበም ሊወጣ ነው።

ማያዬ የተሰኝው የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል የመጀመሪያ አልበም የፊታችን አርብ ይለቀቃል ተብሏል።

ድምፃዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል የመጀመሪያ አልበሟን ሰርታ እንዳጠናቀቀች ዛሬ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግራለች።

ላለፋት አስር እና ከዛ በላይ ዓመታት በኪነጥበብ የሙያ ዘርፍ ውስጥ በትወናና ድምፃዊነት የሰራችው ለምለም ” ማያዬ ” አልበምን ሰርቶ ለማጠናቀቀ ዘጠኝ አመታት እንደወሰደባት ገልጻለች።

የሙዚቃ አልበሙ 12 ዘፈኖችን የያዘ ሲሆን፣ አንድ የኦሮሚኛ ዘፈን ተካቶበታል፡፡ ኤልያስ መልካን ጨምሮ አበጋዝ ክብረወርቅ፣ ሚካኤል ሃይሉ ፣ ታምሩ አማረ ፣ አዲስ ፍቃዱ እና ብሩክ ተቀባ በቅንብር፤

ወንድወሰን ይሁብ፣ ናትናኤል ግርማቸው ፣ ሀብታሙ ቦጋለ፣ ጥላሁን ሰማው በግጥም፤

ኤልያስ መልካ፣ አንተነህ ወራሽ ፣ እሱባለው ይታየው፣ ብስራት ሱራፌል፣ አህመድ ተሾመ፣ ዘርአ ብሩክ ሰማው በዜማ ተሳትፈውበታል ተብሏል።

በሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ሰለሞን ሀይለማርያም፤

በኘሮዲውሰርነት ወንድወሰን ይሁብ ተሳትፈውበታል።

ማያዬ “የሙዚቃ አልበም አርብ ግንቦት 9/2016 ዓ.ም በናሆም ሬከርድስ የዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም በአለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች የሚለቀቅ መሆኑ ተነግሯል።

ለምለም ሀይለሚካኤል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በትያትር ጥበባት ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም ከዚሁ ትምህርት ክፍል በትያትር ፎር ዴቨሎፕመንት የሁለተኛ ደግሪ እጩ ተመራቂ ድምጻዊት ናት፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply