
ምን ዓይነት መረጃ ለማግኘት ፈልገው ወደ ኢንተርኔት ደጃፍ ብቅ ይላሉ? ከዚህ ቀደም ለጥያቄዎ መልስ ፍለጋ በጉግል መረጃ ማሰሻ ላይ ጽፈው ሰዓታትን አባክነው ከሆነ አሁን ብዙ ነገር ተቀይሯል። ለጥያቄዎ ፈጣን መረጃ በማቀበል ረገድ ቻትጂፒቲ (ChatGPT ) የትንፋሽዎ ያህል ቅርብ ነው። በተጨማሪም ሚሊዮኖች መልዕክቶቻቸውን ለማርቀቅ፣ የተለያዩ ጽሁፎችን ለማዘጋጀት፣ የዘፈን ግጥሞችን፣ አልፎ ተርፎም የኮምፒውተር ኮዶችን ለመቀመር ይጠቀሙበታል።
Source: Link to the Post