You are currently viewing My latest news coverage is for Al Jazeera English on Ethiopia's evaporating press freedoms and the arrests of at least 2…

My latest news coverage is for Al Jazeera English on Ethiopia's evaporating press freedoms and the arrests of at least 2…

My latest news coverage is for Al Jazeera English on Ethiopia’s evaporating press freedoms and the arrests of at least 22 journalists and media staffers across the country in 2022. ሰሞኑን ለአል ጀዚራ እየሻከረ ስለመጣው የሃገራችን የፕሬስ ነጻነት ላይ ያተኮረ ዘገባ ለንባብ አቅርብያለሁ። ሚያዚያ 18 እለት የአቃቤ ህግ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ አወል ሱልጣን የመንግስት ጸጥታ ሃይሎች ሃሰተኛ መረጃ እና ጥላቻ በሚበትኑ ላይ በቂ እርምጃ አልተወሰደም ብለው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረው ነበር። ይሄንን መልእክት የሰሙ የሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች በመጪው ቀናት የጋዜጠኞች አፈሳ ይጀምራል ብለው መስጋት ጀመሩ። እንደገመቱት ሆነ። ሚያዚያ 21 እለት የፌዴራል ፖሊስ በ25 የሚዲያ ተቋማት ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ። እንግሊዛዊው የ ዘ ኢኮኖሚስት ዘጋቢ ቶም ጋርድነር ግንቦት 5 እለት የስራ ፍቃዱ ታግዶ ከሃገር እንዲባረር ተደረገ። ከቀናት የሀረር ክልል ቲቪ ጋዜጠኛው ሙህያዲን አብዱላሂ እና የአማራ ድምጽ ዘጋቢው ሲሳይ ጎበዜ ታሰሩ። በግንቦት ወር ብቻ ወደ 19 ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ተቋማት ሰራተኞች በፖሊስ ተያዙ። ከነዚህ መካከል ወደ 12 የሚሆን የተያዙት በአማራ ክልል ነው። በአማራ ክልል ያሉት ሚሊሻዎች እና በመከላከያ መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት መንግስት ሚሊሻዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው ብሎ በመወሰኑ ተቃውሞአቸውን ያሰሙት ሰልፈኞች እና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ አፈሳ አካሄዶ ወደ 4000 ሰዎች ማሰሩን በሮይተርስ ተዘግቦ ነበር። ከታሳሪዎቹ መካከል በዘገባቸውና በትንተና ተቃውሞ ያሰሙት ቢያንስ 12 የሚዲያ ሰራተኞች አሉ። ከነዚህ መካከል 4 የንስር ብሮድካስት እና 5 የአሻራ ሚዲያ ሰራተኞች ከግንቦት 19 ጀምሮ በማረሚያ ቤቶች ይገኛሉ። ባህር ዳር የሚገኘው የአሻራ ሚዲያ ቢሮ እንደ ታሸገ ነው። በፈረንጆቹ 2022 ዓም በአጠቃላይ የኢትዮጵያውያን የሚዲያ ታሳሪዎች ቁጥር ወደ 22 ማደጉንም አጣርተናል። ከነዚህ መካከል በጅጅጋ ከተማ 4 የናባድ ቲቪ ሰራተኞች (ኸርሲ መሃመድ፤ ኢብራሂም ሁሴን፤ መሃመድ ቃሲም፤ ሳልማን ሙክታር) እና በአዲስ አበባ ይሰሩ የነበሩ በቃሉ አላምረው፤ ተመስገን ደሳለኝ፤ የኢትዮ ፎረሙ ያየሰው ሽመልስ፤ የገበያኑ ዩቱብ ቻነል ባለቤት ሰለሞን ሹምዬ፤ የፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ ዘጋቢዋ ሰቦንቱ አህመድ፤ የሮሃ ሚዲያ ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድ እና ለኢትዮ ንቃት ትንተና የምታቀርብ መስከረም አበራም አሉ። የመገናኛ ብዙሃኑ ላይ ያተኮረው አፈሳን በተመለከተ እስካሁን ከመንግስት ምላሽ የሰጠው የአማራ ክልል ቃል አቀባዩ ግዛቸው ሙሉነህን ብቻ ነው። ፌስቡክ ላይ በሰነዘረው ጽሁፍ “የህብረተሰቡን የአንድነት፣ የወንድማማችነትና የመቻቻል ባህልን ማዳከም፣ የብሔርና የሃይማኖት ግጭቶች እንዲፈጠሩ ፅንፈኛ አጀንዳዎችን ማቀንቀን ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል እንጂ በየትኛውም መመዘኛ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ተደርጎ ሊታሰብ አይችልም፡፡” ብለዋል። በጉዳዩ ያነጋገርካቸው የዓለም የፕሬስ ነጻነት የሚቆረቁረው የሲፒጄ CPJ (Committee to Protect Journalists) ተወካይ የሆኑት አንጄላ ክዊንታል በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት መሻከር የጀመረው የዛሬ 3 ዓመታት ገደማ ነበር አሉ። “የሲፒጄ ተቋማችን ባለፉት 3 ዓመት በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ ነጻነት ሁኔታ ኣስጊ ደረጃ ላይ መውደቁን ተከታትለናል።” አሉ። “በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ጦርነት ጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸመው ጭቁና እንዲብስ ምክንያት ሆኗል። በርካታ ጋዜጠኞች ያለምክንያት ታስረው ክስ ሳይቀርብባቸው በእስር ቤት ለረጅም ግዜ ይጉላላሉ።” ጫናውን መቋቋም ያቃታቸው ጋዜጠኞች ስራቸውን እያቋረጡ ከሃገር እየሸሹ ነው። ሌሎች ደግሞ ስራዎቻቸውን ያለ ስማቸው ለእትም ያቀርባሉ። ከ3 ዓመታት በፊት ለውጥ መጣ ተብሎ ጋዜጠኞች ከእስር ቤት ተለቅቀው በርካታዎች ከስደት ወደ ሃገራቸው ተመልሰው አዳዲስ ተቋማት አቋቁመው በነጻነት ለመስራት መብቱ ይከበራል ተብለን የብዙዎቻችን ተስፋ ለምልሞ ነበር። እንደሚታወሰው በ2002 የኢትዮጵያ መንግስት የጸረ ሽብር አዋጅን አጽድቆ ብዙ ጋዜጠኞች አሸባሪ ተብለው ከ10 ዓመት እስከ እድሜ ልክ የሚፈረድባቸው ዘመንም ነበር። የነበረው ተስፋ ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል። ዛሬ ኢትዮጵያ እንደ ድሮ ልማዷ ጋዜጠኞችን ህግ መንግስት በማፍረስ፤ በሃገር ክህደት፤ በሽብርተኝነትንም ጭምር ይወነጀላሉ። ትግራይ ላይ ጦርነት በተጀመረበት የመጀመርያው ሳምንት ነበር 6 ጋዜጠኞች የታሰሩት። ለሃገር ውስጡ የአምባ ዲጂታል Amba Digital – አምባ ዲጂታል ተቋም ዋና ኤዲተር የሆነው ጋዜጠኛ አክመል ነጋሽ ጦርነት የተጀመረበትን ወቅት አዋርቶኛል። “ጦርነት ሲቀሰቀስ መንግስት ለጋዜጠኞች “ወይ ከኛ ጎን ናችሁ፤ ካልሆነ ከአሸባሪዎቹ ጋር ናችሁ” የጆርጅ ቡሽ አይነት መልእክት አስተላልፎልናል” አለ። “መንግስት የሚፈቅደውን ለህዝብ ካላደረስን እንደ ሃገር ጠላት እንደምንቆጠር ግልጽ ነበር። ስራችን በሚገባው ለመስራት አስቸጋሪ እና ለአደጋ አጋላጭ ሆነብን።” መንግስት መረጃ ለማፈን ሲል የፕሬስ አባላት ወደ ጦር ሜዳዎች እንዳይሄዱ ከለከለ። በዚህ ወቅት በትግራይ ክልል ይኖር እና ይሰራ የነበረው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ በመከላከያ ሰራዊት አባላት መገደሉን ሰማን። በስራው የተሰማራ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ሲገደል ዳዊት ከ23 ዓመታት በኋላ የመጀመርያው ነበር። በየካቲት 1990 የወላፈን ጋዜጣ ኤዲተር የነበረው አባይ ሃይሉ በእስር ቤት ታስሮ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ሆስፒታል ገብቶ ህይወቱ አለፈ። በትግራይ ክልል ይፈጸም የነበረው ግፍ እና ስቃይ ለዓለም እየተገለጠ በመጣበት ማግስት በየካቲት 2013፤ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ አስተላልፎ ነበር። “የጁንታው ሞት ያልተዋጠላቸው ከዥንጉርጉር ማህጸኗ የፈለቁ ሰዎች ከሃገራችን ጠላቶች ጋር እያበሩ የተዛቡ መረጃዎችን መርጨት የእለት እንጀራቸው አድርገውታል።” ጋዜጠኛው አክመል ነጋሽ ስለ መልእክቱ ጠይቄው የጠቅላይ ሚኒስቴር መልእክት ለሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች እንደ ማስጠንቀቂያ ተቆጥሮ ከሃገር የተሰደዱ እና ስራቸውን የተዉ ባለሙያዎች ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት ሆነ ብሎ አስረዳኝ። በሚያዚያ ወር ላይ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሃገራችን የሚዲያ ባለስልጣን ( Ethiopian Media Authority – ኢመብባ ) አዲስ አመራርን ሾመ። ከተሾሙት አባላት መካከል የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል እና የፖለቲካ እስራኛ የነበረው ዮናታን ተስፋዬ የሚዲያ ባለስልጣን አዲሱ ምክትል ዳይሬክተር ሆነ። ዮናታን ተስፋዬ በጦርነቱ ወቅት በመቶ ሺህዎቹ ለሚቆጠሩ የፌስቡክ ተከታዮቹ በቢቢሲ እና በአዲስ ስታንዳርድ የተቀጠሩት ጋዜጠኞች “ባንዳዎች” በመሆናቸው መታሰር ነው የሚገባቸው የሚል መልዕክት አስተላልፎ ነበር። ይሄን መሰል ጸያፍ መልእክት ካስተላለፈ ከወራት በኋላ እኚህ ግለሰብ ሚዲያን የሞቆጣጠር ስልጣንን ተረከበ። አዲሱ አመራር ስራውን ተረክቦ መንግስትን የሚተች ባለሙያን ማሳሰር፤ የስራ ፍቃድ መንጠቅ፤ ከሃገር ማባረር፤ ቢሮ ማሸግ፤ የቅጂ እና የቀረጻ መሳሪያ መዝረፍ ስራውን አደረገው። ፖሊስ ጋዜጠኞች ጎትቶ ወደ እስር ቤት መውሰድ ልማዱ ሆነ። ሰኔ 23 እስከ 25 በነበረው የ48 ሰዓታት ውሎ ብቻ በአጠቃላይ 21 የሚዲያ ሰራተኞች ከአውሎ ሚዲያ እና ከኢትዮ ፎረም የተያዙበት ወቅት ነበር። የፈረንጆቹ 2021 መጠናቀቅያው ላይ በአጠቃላይ 46 ጋዜጠኞች ታስረው ነበር። ከታሳሪዎቹ መካከል በኦሮሚያ ክልል እየተፋፋመ በመጣው ጦርነት እና በክልሉ እስከፊ ሆኖ እየመጣ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ችግር ሽፋን ይሰጡ የነበሩት የኦሮሚያ ኒውስ ኔትወርክ Oromia News Network ጋዜጠኞች ደሱ ዱላ እና ቢቂላ አመኑ ይገኛሉ። ሁለቱ እስካሁን ያለፉት 6 ወራትን በእስር ቤት ያሳለፉ ሲሆኑ ህግ መንግስትን ለማፍረስ ሰርታችዋል ተብለው ተከሠዋል። ክሱ የሞት ፍርድ ማስከተል የሚችል ነው። ለጋዜጠኞች ያሁኑ ወቅታዊ ሁኔታው ከቀድሞ የነበረው የ27 ዓመታት ዘመን የሚብስ ሆኗል” ብለው ተናገሩ በአሻራ ሚዲያ Ashara Media – አሻራ ሚዲያ የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ታዘበው አሰፋ። ተቀማጭነቱ በባህር ዳር ያደረገው አሻራ ሚዲያ 5 ባልደረቦቹ በእስር ቤት ይገኛሉ። የአሻራ ሚዲያ ጋዜጠኞች ቀለሙ ገላጋይ፤ ዳንኤል መስፍን፤ ጋሻዬ ንጉሴ፤ ጌትነት ያለው እና ሃብታሙ መለሰ ከታሰሩበት ግንቦት 11 እለት ጀምሮ በጠበቃ ወይም በቤተሰብ እንዳልተጎበኙ አቶ ታዘበው አስረድተውኛል። “አሻራ ሚዲያ በአማራ ክልል ያለው የሙስና ችግር በተደጋጋሚ ሽፋን በመስጠታችን እና የክልሉ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የማይዘግበውን ለመዘገብ ወደ ኋላ ባለማለታችን ከዓመት በላይ ይሆኗል ሊያዘጉን ከፈለጉ። መንግስት በጋዜጠኞችና በግል ሚዲያ ላይ አፈና መፈጽሙን መርጠዋል። ይሄ ግን የተሳሳተ አከሄድ ነው። እንደውም ጭቁን ህዝብን ወደ ጥትቅ ትግል ሊያገፋፋው የሚችል ድርጊት ነው።” ብለዋል አቶ ታዘበው። ሙሉ ዘገባው በእንግልዘኛ ቋንቋ በአል ጀዚራ ድረ ገጽ ያገኙታል። የፕሬስ ነጻነትን በተመለከተ የማንደራደርበት መብታችን ነው። አንዳንች ሰዎች ሚዲያ በማፈን ሃገር ተጠቀመ አንድነታችን ጠነከረ ይላሉ። ያለ ነጻ ፕሬስ ሃገር ውድቁቷን የምናፋጥንበት የገዢዎች መጫወቻ ትሆናለች። አቋማችን አንድ እና አንድ ሊሆን ይገባል። አፈናውን በጽኑ ማውገዝ ሰብዓዊነት ነው። ያለ ምንም ወንጀል የታሰሩት የሙያ ባልደረቦቼ በሙሉ ይፈቱ! ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም! #JournalismIsNotaCrime ! @Zecharias Zelalem አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ

Source: Link to the Post

Leave a Reply