በኒውዚላንድና አውስትራሊያ ኗሪ ከሆኑ የአማራ ማህበርሰብ አባላት የተሰጠ የአቋም መግለጫ

በኒውዚላንድና አውስትራሊያ ኗሪ ከሆኑ የአማራ ማህበርሰብ አባላት የተሰጠ የአቋም መግለጫ

ህዳር 18፣ 2013 ዓ.ም.

  • እኛ በኒውዚላንድ እና አውስትራሊያ የምንኖር የአማራ ተወላጆች፤ በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ (ትህነግ)ና በኦነግ ሸኜ አሸባሪ ቡድን አማካይነት እየተፈጽመ ያለውን በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጽመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንድጀል አጥብቀን እናውግዛለን። እነዚህ ወንጀለኛ ቡድኖች በፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ አድርጎ ለማቅረብ በሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ለመሳተፍና ለማገዝ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን።

 

  • በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፕብሊክ መንግስት በእነዚህ ወንጀለኛ ቡድኖች ላይ ከሚወስደው ህጋዊ እርምጃ ባለፈ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በማያሻማ ቋንቋ የዘር ማጥፋት ወንጀል መሆኑን እንዲመሰክርና በግልጽ እንዲያውግዝ፤ ወንጀሉም በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ካውንስል የሚጣራበትን ሁኔት እንዲያመቻች አጥብቀን እንጠይቃለን።

 

  • በአሁኑ ስዓት በትህነግ ላይ በኢዮጵያ መንግስት ሀገር መከላከያ ሠራዊት እየተፈጸመ ያለው ህግና ሥርዓት የመቆጣጠር ዘመቻ አጥብቀን እንደግፋለን። ይህን ፀረ ሰላም የሆነ አጥፊና አሸባሪ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲደመሰስና ወንጀለኛ የሆኑ ግለሰቦች ተለይተው ተጠያቂ እንዲሆኑ እንጠይቃለን።

ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በአማራ ህዝብ ላይ የፈጸማቸው ሁሉን አቀፍ ዘር የማጥፋት፣ የማደህየትና ታሪካዊ ርስት የሆኑትን ወልቃይት ጠገዴንና ራያን በጉልበት በመንጠቅ እና ነባር ተወላጆችን በአሰቃቂ ሁኔት በመግደልና በማፈናቀል በራሱ ፖለቲካዊ አስተዳድር በሃይል ተቆጣጥሮቸው ቆይቷል። በመሆኑም የወልቃይት ፀገዴና የራይ መሬቶች ለእውነትኛ ባለርስቶቹ የወልቃይትና ራያ አማራዎች እንዲመለሱና አካባቢዎቹም በቋንቋ፣ በባህል፣ ታሪክና ኢትዮጵያዊ ስነልቦና አንድ ሆነው ወገናቸው የአማራ ክልል አስተዳደር ይካተቱ ዘንድ አጥብቀን እንጠይቃለን። ለዓመታት ያለ ማቋረጥ የደም ዋጋ እየተከፈለበት የቆየው ይህ የአማራ ማንነት ጥያቄ በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ምላሽ ያገኝ ዘንድ በመላው ዓለም የምትገኙ የአማራ ተወላጆችና እውነት ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተደራጀ መልኩ እንቅስቃሴ ታደርጉ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

 

ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!

Leave a Reply