#UPDATE
የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ በተደረገው ማሻሻያ የ50 ሳንቲም ጭማሪ ተደረገ፡፡
አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ ተግባራዊ የሚሆነው ከነገ ጀምሮ ነው፡፡
የታሪፍ ማሻሻያው እንደሚያሳየው የተደረገው ጭማሪ 50 ሳንቲም ነው፡፡
የጥር ወር ነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የአገልግሎት መስጫ የዋጋ ታሪፍን ማሻሻያ ጥናት ተደርጓል፡፡
በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ ግምት ውስጥ በማስገባት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በማሻሻያው መሰረት ለሚኒባስ የታክስ ተሸከርካሪዎች÷ የጉዞ ርቀት በኪሎ ሜትር እስከ 2 ነጥብ 5 ርቀት በነባር የክፍያ ታሪፍ 3 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው በተስተካከለው ታሪፍ 4 ብር፣ ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5ኪሎ ሜትር ርቀት 6 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ታሪፍ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 7 ብር ሆኗል፡፡
ይሁንና ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5ኪሎ ሜትር ርቀት 10 ብር የነበረው ታሪፍ በተመሳሳይ 10 ብር ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡
ኢትዮ አፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም