Update/የተሻሻለ! በምዕራብ ወለጋ ጊንቢ ዞን በጉሊሶ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች አስገድደው በሰበሰቧቸው አማራዎች ላይ በፈፀሙት የጅምላ ጭፍጨፋ ከ60 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ህይወታቸው…

Update/የተሻሻለ! በምዕራብ ወለጋ ጊንቢ ዞን በጉሊሶ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች አስገድደው በሰበሰቧቸው አማራዎች ላይ በፈፀሙት የጅምላ ጭፍጨፋ ከ60 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ህይወታቸው…

Update/የተሻሻለ! በምዕራብ ወለጋ ጊንቢ ዞን በጉሊሶ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች አስገድደው በሰበሰቧቸው አማራዎች ላይ በፈፀሙት የጅምላ ጭፍጨፋ ከ60 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ከ20 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆሰሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ወለጋ ጊንቢ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ መትረጊዬስና ሌሎች የቡድን መሳሪያዎችን በታጠቁ በግምት ቁጥራቸው 60 የሚሆኑ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ትናንት ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት አስገድደው በት/ቤት በሰበሰቧቸው አማራዎች ላይ የቦንብና በጥይት የጅምላ ጭፍጨፋ መፈፀማቸውን መዘገባችን ይታወሳል። የዐይን እማኞች ዛሬ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም 2 ሰዓት ላይ የጅምላ ጭፍጨፋው በተፈፀመበት ት/ቤት ብቻ 60 አስከሬን እንዳገኙና ሌሎች 20 የሚሆኑት ደግሞ በከባድና በቀላል መቁሰላቸውን አረጋግጠዋል። በጅምላ የተገደሉትና የቆሰሉት አማራዎች ቁጥራቸው ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ነው ምንጮች የተናገሩት። አይደለም ከኦነግ ሸኔ ጥቃት የሚከላከል ነውና አስከሬን የሚያነሳ መንግስት አጥተናል ሲሉ ነው ከጭፍጨፋው የተረፉት ወገኖች የተናገሩት። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ አንድም መከላከያም ሆነ ሌላ የመንግስት አካል በስፍራው አለመድረሱን የተናገሩት ወደ ጫካ ሸሽተው ያደሩት ነዋሪዎች አስከሬኑና የቆሰሉትን አንስተው ወደ የት እና እንዴትስ እንወስዳለን በሚል በከፍተኛ ሀዘን፣ስጋትና ግራ መጋባት ስሜት ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። በግፍ ከተጨፈጨፉት መካከልም እንደአብነት ሞገስ መልካሙ፣የአቶ ሞገስ የኮሌጅ ተመራቂ ልጁ ተማሪ ተከታይ ሞገስ፣እንዳለ እባቡ፣ተላከ ጌጤ፣ደመቁ ካሳ፣ ወ/ሮ እናኑ ሲሳይ፣ቄስ መሰለ እና ሌሎችም ይገኙበታል። አሁንም እባካችሁ ስለወገን ብላችሁ የሚል የድረሱልን ጥሪ አስተላልፈዋል። በድምፅ የተደገፈውን ዝርዝር መረጃ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply